Monday, July 22, 2013
ሰው በአፉ እንጂ በእጁ አያነሳህም
በከተማችን
ውስጥ በጣም ከምወደው ስፍራዎች መካከል አንዱ ብሔራዊ አካባቢ ነው፡፡ ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ… እነ ክሮኮዳይል፣
ናሽናል ካፌ መደዳ… ከወጣት እስከ አዛውንት፣ ከሰራተኛ እስከ ጡረተኛ እግሩን አነባብሩ፣ ቡና እየጠጣ ጋዜጣ
የሚያነብበት መደዳ…
በጣም የሚገርመኝ ያ መደዳ ሁልጊዜም አንድ አይነት ምስል ነው ያለው… የተነባበሩ እግሮች፣ የተዘረጉ እጆች፣ የትኩስ ቡና ሽታ፣ የተዘረጉ ጋዜጦች…
ብሔራዊ አካባቢ ሰው ሲቀጥረኝ በጣም ነው ደስ የሚለኝ… በቃ እገሬን አነባብራለዋ፣ በጋዜጣ ቁመት ልክ እጄን
እዘረጋለው፣ ከዛም ቡናዬን ፉት፣ ፉት እያልኩ አላፊ አግዳሚውን እገረምማለው፤ የዚያ የሚያምር ትዕይንት አካል መሆን
አስደሳች ነገር ነው፡፡
ታዲያ ከትላንት በስቲያ ነው፣ አንድ ጓደኛዬ ብሔራዊ አካባቢ እንገናኝ ሲለኝ
ፈነጠዝኩ… ቀድሜ ደረስኩና ጫማዬን አስጠረኩ፤ ምክንያቱም በቆሻሻ ጫማ እግር ማነባበር ይደብራላ! የውቡን ትዕይንት
ቀለም ያጎድፋል፡፡
ጓደኛዬ እስኪመጣ ጋዜጣዬን ገዝቼ ናሽናል ካፌ በር ላይ ተሰየምኩ፤ በጋዜጣው
ቁመት ልክ እጄን ዘረጋሁ (እጄን ስዘረጋ በቲሸርቴ በኩል ወደ ብብቴ የገባው ቀዝቃዛ አየር ምናምን አልላችሁም ያው
ዲስከስቲነግ ስለሆነ ማለቴ ነው) ከዛም እግሬን አነባብሬ ቡና እንደወረደ አዘዝኩ… ቡናዬን ፉት እያልኩ አልፎ አልፎ
በጋዜጣው አናት ወጪ ወራጁን እቃኛለሁ…
አንድ ፅሁፍ አንብቤ እንደጨረስኩ ለአፍታ እረፍት አይኔን በጋዜጣው አናት ሽቅብ ከፍ አድርጌ አላፊ አግዳሚውን ማጤን ጀመርኩ…
አንድ ወጣት ላይ አይኔ አረፈ ጥድፍ፣ ጥድፍ እያለ እየተራመደ ነው፤ በቅጡ ከፍ ዝቅ አድርጌ ሳላየው ከመቅፅፈት…
የተፈታ የጫማ ማሰሪያው አደናቅፎት በእርምጃው ፍጥነት መሬት ላይ ተዘረገፈ… ይህን ጊዜ የሁሉም ጋዜጣ አንባቢዎች
አይን ወጣቱ ላይ አረፉ… የተወሰኑት "አይዞህ!" ግማሾቹ "ወንድሜን!" ሌሎቹ "ተነስ! ተነስ!" ብለውት መልሰው
አይኖቻቸውን ጋዜጦቻቸው ላይ ቸከሉ፡፡
ወጣቱም ፊቱ ላይ የአፍረት ፈገግታ እያሳየ
ፍንጥር ብሎ ተነስቶ ሱሪውን ካረጋገፈ በኋላ የጫማ ማሰሪያውን አስሮ በፍጥነት ከፊታችን ተሰወረ… ከእኔ ህሊና ግን
ሳይሰወር ቀረ… በወቅቱ የነበረውን ትዕይንት ሰፋ አድርጌ አሰብኩት…
በቃ! ህይወት ማለት እኮ እንዲህ
ናት! አልኩ… ላይ፣ ታች ትላለህ፣ ትውተረተራለህ… በመሃል እንደ ወጣቱ ልጅ የራስ ጫማ ክር፣ አልያም በሰው ክር
ተደናቅፈህ ትወድቃለህ፤ ታዲያ ወንድም ሆይ… ማንም አደናቀፈህ፣ ምን ሁሉም እግሩን አነባብሮ "አይዞህ!" "ተነስ!"
ሊልህ ይችላል አንጂ እጁን አይሰጥህም (እሱንም ስበህ የምትጥለው ይመስል) ማንም አያነሳህም፤ በራስህ ሀይል
ተነስተህ፣ አባራህን አራግፈህ፣ ያላላውን አጥብቀህ ጉዞህን መቀጠል ነው…
አይግረምህ… ህይወት
እንደዚህ ናት፤ እግሩን ባነባበረ ታዛቢ ፊት የምትወድቅና የምትነሳባት፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ! አንድ ነገር
ልምከርህ… በህይወት ሩጫህ ባንተም ይሁን በሰው ክር አደናቅፎህ ብትወድቅ፣ አንሺ አገኛለው ብለህ ወድቀህ
እንዳትቀር! አወዳደቅህ ምንኛ ቢከፋ እንደምንም ብለህ ተፍጨርጭረህ ተነስ! ሰው በአፉ እንጂ በእጁ አያነሳህምና!
"መሮጥ ቢያቅትህ፣ ተራመድ፣ መራመድ ቢያቅትህ፣ ዳህ፣ መዳህ ቢያቅትህ፣ ተንፏቀቅ…" ነገር ግን በፍፁም ወድቀህ
እንዳትቀር ማንም ሊያነሳህ እጁን አይሰጥህምና!
ጉዞ አልባው የጉዞ ማስታወሻ
ይቺ የጉዞ ማስታወሻ ከሌሎች የጉዞ ማስታወሻዎች በእጅጉ ትለያለች፤ "እንዴት?" አትሉም…
ሲጢጢጥ…. በናታችሁ… ቆይ… አንዴ… ታይም አውት… ወደ ዋናው ፅሁፌ ከመግባቴ በፊት አንድ ነገር ልበላችሁ…
መቼም የመጀመሪያዋን አረፍተነገር ስታነቡ… "በምን ይሆን ይቺ የጉዞ ማስታወሻ የተለየችው?" ብላችሁ መጠየቃችሁ
አይቀርም፤ ወይም ደግሞ… "እቺማ እንደ ዘንድሮ ማስታወቂያ አገባብ ማሳመሪያ ናት፣ ለሽያጭ ናት…" ብላችሁ
ይሆናል፡፡ አትፍረዱብኝ… ዘንድሮ እኮ ሁሉ ነገር ውድድር ሆኗል፤ ሁሉ ነገር ሽያጭ ሆኗል…
ኢንፎርሜሽን እንኳን ሳትፈልግ በግድህ የምትጋትበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የቱን አንብበህ፣ የቱን መተው እንዳለብህ
ለመምረጥ እንኳን ፋታ አታገኝም፤ ዞር ስትል ጋዜጣ ነው፣ ዞር ስትል መፅሄት ነው፣ ዞር ስትል እንትናዬ እቺን
ፍላየር ነው፣ ግድግዳው፣ ታክሲው፣ ባሱ፣ ልብሱ… ሁሉ ነገር ማስታወቂያ ነው፣ መረጃ ነው፡፡
ታዲያ
አንዳንዴ… ሁሉ ነገር ይሰለችህና የፅሁፍ ጋጋታ የሌለው ዕይታ ናፍቆህ ወደ ሰማይ ስታንጋጥጥ ሰማይ ላይ ተሰቅለው
ሰማይ አላሳይ የሚሉ፣ ሰማይ ጠቀስ ቢልቦርዶች ያጋጥሙሃል… በቃ እንደለመደክው ሳትወድ በግድህ ወደ ሐበሻዊነትህ
ትመለሳለህ… አንገትህን ትደፋለህ… ያለ ቅንነትህ ቅን ትመስላለህ፤ የወደቀ ዕቃ የምትፈልግ ይመስል በግድ አንገትህን
ቀብረህ ትርመሰመሳለህ…
እናም ይህ ሁኔታ ባለበት፣ እንደ ፀሃፊ፣ ለምትፅፈው ፅሁፍ አንባቢ አገኝ
ይሆን ብለህ መጠየቅህና መስጋትህ አይቀርም፡፡ ለዚህ ነው ምንግዜም ፅሁፌን ስጀምር፣ የመጀመሪያዋን አረፍተነገሬን
ረጅም ሰዓት ወስጄ የማስበው፡፡ አስቤ፣ ሰርዤ፣ ደልዤ በቃ በምርጥ አረፍተነገር እገባለሁ… የዛሬው ግን እንደዛ
አይደለም፣ በቃ ፅሁፉ እራሱ ለየት ያለ ነው… ብትፈልግ አንብብ ባትፈልግ ተወው! አልልህም… አንብበው… ገዳይ ወግ
ነው፡፡
ስለዚህ ደግሜ እላችኋለው… "ይህች የጉዞ ማስታወሻ ከሌሎች የጉዞ ማስታዎሻዎች በእጅጉ ትለያለች" አሁን በቀጥታ ወደ ነገሬ ልገባ ስለሆነ… "እንዴት?" በሉ… ነገሩ እንዲህ ነው…
የጉዞ ማስታወሻ ሲባል አንድ ሰው ወደ አንድ ቦታ በሄደበት ወቀት ያጋጠመውን፣ ያስተዋለውን፣ የሰማውን፣
ያነበበውን… ሌላም ሌላም ነገሮችን አክሎ፣ ውብ ስነፅሁፋዊ ጥበብን አላብሶ የሚያቀርበው ፅሁፍ ነው፡፡ ይህች የጉዞ
ማስታወሻዬ ግን እኔና ጓደኞቼ አንድ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለን፣ በምርቃና ባቡር ተሳፍረን፣ በሃሳብ ሰረገላ ተጉዘን፣
ያየናቸውን፣ የተገነዘብናቸውንና፣ የተዝናናንባቸውን፣ ግብብዳ የሳቅ እንባ ዘለላዎችን የተረጫጨንባቸውን ጉዳዮች
ለናንተ የማጋራባት፣ ጉዞ አልባ የጉዞ ማስታወሻ ናት፤ ንሱማ… ዝለቁ…
ወደ ጉዟችን ከመዝለቃችን በፊት… አብረውኝ የሚጓዙትን ተሳፋሪዎች በጥቂቱ ላስተዋውቃችሁ…
ሼባው- ሼባው ‘‘እድሜው ትልቅ ነው…'' እያልን የምናማው ጓደኛችን ነው… የምር ግን… በቅንፍ ውስጥ… ድምፄን ዝቅ አድርጌ… ይቀቅመናል!
ሌላው ሰላ ነው፤ ሰላ በቃ መመርቀን የሚወድ፣ የግሩፓችን ዋና የቀልድ አከፋፋይና ብቸኛ አስመጪ ነው፡፡
ጎሹ ደግሞ እንደ ጎሽ ትከሻው ሰፊ እና በጭንቅላቱ ሳይሆን በቀንዱ የሚያስብ ብለን የምናሞካሸው ጓደኛችን ነው፡፡
አለችላችሁ ደግሞ ኤም.ፒ.ስሪ (mp3)፡- mp3 ሴት ጓደኛችን ስትሆን በቃ ነን እስቶፕ ቀዳጅ ናት፣ የወሬ ቋት…
ሌላዋ የግሩፑ አዝናኝ ደግሞ ግራ ናት፤ ግራ ወሬዋ ሁላ ግራ የገባውና የራሶችዋን ቃላቶች በመፍጠር የምትታወቅ ናት፤ በሷ አመርኛ መልሼ አማርኛዋን ስገልፀው… ‘አማርኛዋ የተንቦራደሰ ነው…'
ቀንዶ- ቀንዶ በተረበኛነቱና በአረቄ አፍቃሪነቱ የሚታወቅ ጓደኛችን ነው…
ፌዶ- ሃርደኛ ጀለሳችን ናት፣ ከመሬት ተነስታ ፊትዋን የምትፈጠፍጥ ወይም በኛ አገላለፅ ዝም ብላ ጓ! የምትል…
ሱፔ ደግሞ የራሱ ቋንቋ ያለው ወጣ ያለ ጓደኛችን ነው…
በሉ በሉ… እኔ ሃተታዬን ሳበዛ ጉዞው ሊጀምር ነው፤ እኔን ጨምሮ አስር ተጓዦች ባቡሩ ላይ ተሳፍረናል… እንደለመድኩት በመስኮት በኩል ተቀምጫለሁ… አብራችሁኝ ተጓዙ….
ሰላ፡ አያምርም? እስቲ እየው በናትህ! እንዴት አባቱ ለምለም ነው ባክህ… ደግሞ ዝንፍልፍል ማለቱስ የሚናቅ ነው? ካካካካ….
ጎሽ፡ ፐ! ምርጥ ነው… አንተ እስከ ዛሬ የት ሆነን ነው… እዚሁ አጠገባችን ሆኖ ሳናየው… ተሸውደናል! ሁለተኛ ከሉሉ በለጬ አንገዛም? እየው እስቲ፣ እጁ እራሱ… አንደኛ ነው… በዛ ላይ ቅላቱ…
ሱፔ፡ ኢግሩስ እራሱ…
ሁላችንም ካካካካካ… ሱፔ ከወሬው ይልቅ የአነጋገር ዘይቤው (አክሰንቱ) ሽንታችንን ነው የሚያስጨርሰን፡፡ አማርኞቹን እያንሻፈፈ ነው የሚያወራቸው፡፡
ቀንዶ፡ አቦ ሰዓት የለም… አምጣው ባክህ እንቃምበት… ዝም ብለህ አታሽሞንሙነው…
ኤም.ፒ.ስሪ (mp3)፡ ቀንጥሱልኝ?
ግራ፡ እኔ ልበጥስልሽ?
ባቡሩ በሳቅ ድብልቅልቁ ወጣ... ሰላ አልቻለም፣ መሬት ላይ እየተንከባለለ እየሳቀ ነው…
ሼባው፡ ሳቁን በአግባቡ ሳይጨርስ… አንቺ በጣሽ! አይሻልሽም እኔ ልሸልቅቅልሽ…
እንደገና ሌላ ረጅም ሳቅ…
ሱፔ፡ እቺ… ብጣሻም… ባሳቅ ፈረፈረችን እኮ…
ፌዶ እንደልማዷ ጓ! ብላለች፤ ሁላችንም ከልባችን እየሳቅን ነው፤ እሷ ግን አልፎ አልፎ ጥርሷን ብልጭ እያደረገች ተቆልላ ተቀምጣለች፡፡
ሰላ፡ አቦ ፌዶ ፈታ በይ… ቱታ ልበሺ… የምን ጓ! ማለት ነው…
ፌዶ መልስ አልሰጠችም፤ ከጥፊ ባልተናነስ ግልምጫ ገርምማው ሲጃራዋን ለኮሰች… ጉዞው ቀጥሏል… ባቡሩ በጭስና በወሬ
ታፍኗል… mp3 እንደ ልማዷ ‘‘አንዴ ስሙኝማ…'' እያለች የተጓዡን ቀልብ ለመሳብ ትቅለበለባለች…
ጎሽ፡ አረ! ሽንቴን ወጠረኝ…
ይህን ጊዜ ሁላችንም እረፍት ለማድረግ ወሰንን… ሽንቱ የመጣበት ሽንት መሽኛ ፍለጋ… ትኩስ ነገር የሚፈልገው ሲኒ
ማንኳኳት… ስልክ የሚደውለው ስልኩን ይዞ ጎምለል ጎምለል… እኔም የጉዞ ማስታወሻዬን በምስላዊ መረጃ ለማስደገፍ
መቅረፀ-ምስሌን ብድግ አድርጌ… ቀጭ… ቀጭ… ቀጭ… ከደቂቃዎች በኋላ ተጓዦች ከየዕረፍቶቻችን ተመለስን… ወደ አንድ
መንፈስ…
ቀንዶ፡ እስቲ የጉዞ ከፍታ አሳውቁ… ምርቃና ሌቭል ቼክ… ቼክ… ቼክ…
ግራ፡ እስውቅ
ሼባው፡ እኔ ክላውድ ናይን ላይ ነኝ…
ጎሹ፡ በሌቭል ከሆነ የኔ ሬድ ሌቭል ነው… ትንሽ ስቆይ ደግሞ ብላክ ሌቭል ይሆናል…
ካካካካ… ባቡሯ እንደገና የሳቅ ጭስ አፈናት… የጎሹ እንግሊዘኛዎች አድክም ናቸው… እንግሊዘኛና እሱ እጅና እግር ናቸው… አይገናኙም…
ሱፔ፡ እስቴኪኒ ያየ አለ?
ግራ፡ አ-ላ-የ-ን-ም እባካችሁ… መሃረቤን አያችሁ የሚለው ትዝ ብሎኝ ነው…
ፌዶ፡ አንቺ እብድ…
ቀንዶ፡ የምሳው ሽሮ ጥርስህ ውስጥ ተቀርቅሮ ነው?
ሱፔ፡ አይ! ቅድም ያጨስኩት ሲጋራ ጭስ ተቀርቅሮብኝ ነው…
እንደገና ሌላ ሳቅ…
mp3፡ ስሙኝማ…
ሰላ፡ አረ! ቆየን ከሰማን የሚጋግርብን አጣን እንጂ…
ካካካካ… ካካካካ… ካካካካ…
ወሬው ደርቷል… ይቀለዳል… ይሳቃል… በቃ ሙሉ መንገዱ አዝናኝ ነው… ሁሉም እብድ ናቸው፤ በቃ ጤነኛ ወሬ የሚያወራ
የለም፡፡ mp3 በሰላ ትረባ ተናዳ ነው መሰለኝ ለተወሰነ ደቂቆች ‘ስሙኝማ' አላለችም… ኡፈይ ብለናል…
ግራ፡ አንተ ሰላ! mp3ን በቅድሙ ትረባህ mp0 (አም.ፒ.ዜሮ) አደረ‘ካት እኮ … አላወራም አለች…
ካካካካ… ካካካካ… ሰዓሊው እንደለመደው መሬት ላይ እየተንፈራፈረ ነው… ሼባው መሬት በእጁ እየደበደበ ይንከተከታል…
ምን አለፋችሁ… በቃ አንዲሁ በሳቅ አንጀታችን እንደቆሰለ፣ እንዲሁ ‘ስሙኝማ' እንደተባልን፣ እንዲሁ ጓ! እንደተባለብን፣ የጉዛችን መዳረሻ ተቃረበ…
ሱፔ፡ በሉ ደረስናል እንውረድ…
ጎሹ፡ እራት የሚበላ አለ? …ሁሉም ዝም…
ቀንዶ፡ በቃ ወደ አልጋችን ከመሄዳችን በፊት… አንዳንድ እንበል… ይህን ጊዜ ሁሉም እቃውን እየሸካከፈ፣ እየተጣደፈ ወረደ…
በሉ! ለዛሬው ይብቃን፤ እኔም ክፍሎቼን ዕቃዎቼ ውስጥ አስገብቼ… ምንድን ነው ያልኩት? እእእ… ዕቃዎቼን እክፍሌ
አስገብቼ አንድ ሁለት ልል ነው… ማለቴ ነው… ‘መረቀንኩ እንዴ?'… በሉ በሉ… አፌ ተሳሰረ… ጉሮሮየም ደርቋል…
ቀላል ጠምቶኛል… በሌላ የጉዞ ማስታወሻ እስክንገናኝ… ሰላም!
ከተቀማጭ ወደ ሯጭ ፕሬዝዳንት
የሆነ ሰሞን ከተማችን ላይ ኢንፎቴይመንት የምትል የፅሁፍ ውጤት ነበረች… በነገራችን ላይ
‘ኢንፎቴይመንት’ኢንፎርሜሽንን እና ኢንተርቴይመንትን በማዋሃድ የተፈጠረች ቃል ነች... እኔ ደግሞ ዛሬ የማጫውታችሁ
ፖሊቴይመንት የምትባል ወግ ነው ፖለቲካን ከኢንተርቴይመንት አዋህጄ…
ዘንድሮ መቼም ጦቢያችን አልተቻለችም፣ በድል ላይ ድል፣ በሪከርድ ላይ ሪከርድ… አዳዲስ አስፓልቶች፣ አዳዲስ ካቢኔ፣ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር… የአባይ ግድብ፣ የከተማ ባቡር… ሌላም፣ ሌላም…
አዲስ አበባማ አይናችን እያየ እንደ ስሟ አበባ ልትሆን ነው… ከጥቂት አመታት በኋላ ደግም አገራችን አራሷ የማናውቃት ኢትዬጲያ ልትሆንብን ነው…
በተለይ በዚህ አመት ልክ እንደ ዋልያዎቹ ማልያ፣ ‘ኢትዮጲያዊነቴ ኩራቴ’ የሚለው ቲ-ሸርት እንደ ጉድ እየተቸበቸበ ይመስለኛል…
ለምሳሌ… ይሄ የሰሞኑ የካቤኔ ሹም ሽረት… ሲቪሪ ሜሞሪ ሎስ ቢያጋጥመኝ እንኳን ስማቸውን የማልረሳውን የሚኒስቴሮች ስም ከዋናው መድረክ በስተጀርባ ያደረገበት ሁኔታ ነው ያለው… እውነቴን እኮ ነው! ለውጥም በሉት ልወጣ... የስንት ሚኒስቴሮችን ስም እንደ አዲስ እንደምንሸመድድ አስባችሁታል?
ድሮ፣ ድሮ "እገሌ የሚባል ሚኒስቴር መ/ቤት የት እንደሆነ ታውቃለህ?" ብሎ ሰው ሲጠይቀኝ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ስም ይልቅ የሚኒስቴሩ እና የሚኒስቴር ድኤታው ስም ነበር ቶሎ ወደ አይምሮይ ከች የሚለው… የሚኒስቴር ስምና የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስም ልክ እንደ አረፍተነገር የማይለያዩ ነገር ይመስሉኝ ነበር… ልክ "አበበ…" ሲባል "…በሶ በላ" የሚለው እንደሚመጣብኝ አይነት…
ይሄ… አዲስ ነገር በመፅሄት እንጂ በህይወቱ የናፈቀው ህዝብ በአሁኑ ሰዓት አዲስ፣ አዲስ ኢትዬጲያ እየሸተተችው ያለበት ሁኔታ ነው ያለው.. አስቡት እስቲ እቺን ጋዜጣ እንኳን ሳይቀር በባቡር ላይ ሆናችሁ የምታነቡበት ጊዜ እኮ እውን ሊሆን ነው…
መቼም… ያልሰማህ ስማ፣ የሰማህ አሰማ ነውና ብሂሉ… ከተማው ላይ የሚናፈሰውን አዲስ ወሬ ሰምታችኋል? ሰምታችሁ ካልሆነ… ቀጣዩ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የመሆን እጣ ፋንታ ሊደርሳቸው ከሚችሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ… እውቁ፣ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ መሆኑን በሰፊው እየተናፈሰ ነው…
ይህ ወሬ አሉባልታ ከመሆን አልፎ እውነት-ባልታ ከሆነ ለሀይሌም ይሁን ለአገራችን ትልቅ ስኬት ነው፤ እኛም ልክ እንደ አማሪካ ‘የስ ዊ ካን’ ወይም እንደ ሀይሌ ‘ይቻላል!’ የምንልበት ጊዜ ሊመጣ ነው ማለት ነው…
‘ዌል እንግዲክ’ እንደዛ ሊሆን ነው ብለን እናስብና… ምን አይነት ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ ወደሚለው እንሂድ…
እስከማስታውሰው ድረስ… ኢትዬጲያ ፓርሊያመንታሪ ስርዓት ተከታይ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዬጲያ ፕሬዘዳንት ስራ ምንድነው ብላችሁ ብትጠይቁኝ… አንደኛ- አሪፍ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ለአዲስ አመት እንዲሁም ለህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማንበብ፤ ሲቀጥል፣ የምረቃና የሽልማት ፕሮግራሞች ላይ መሳትፍ ነው… እነዚህም ዝግጅቶች ላይ አጭር ንግግር አድርጎና ባስ ካለም ሪቫን ቆርጦ ቁጭ ማለት ነው… ባጭሩ በፓርላመንተሪያን አገራት ያለው የፕሬዝዳንት የስራ ሃላፊነት የአገር ተጠሪነት እንደመሆኑ ‘ቁጪያ’ እንጂ ያን ያህል ሩጫ አይበዛውም…
እንግዲክ… ሀይሌ ፕሬዝዳንት ሲሆን እንዴት አስችሎት ሊቀመጥ ነው? እስቲ አስቡት… ቤተ-መንግስቱ ውስጥ የመሮጫ ትራክ ሊሰራ ነው ማለት ነው… በቀን ሁለቴ ጠዋትና ማታ ትሬይኒንግ… ስራ ካልተደራረበ ደግሞ በሃይሌ ፅናት ቀኑን ሙሉ ግቢዋን ሊዞራት ነው…
እርግጠኛ ነኝ ሀይሌ የአዲስ አመት የመልካም ምኞት ሲሰጥ እንደ ቀደምት ፕሬዝዳንቶች አሪፍ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ሳይሆን… ልክ የመሮጫ ትራክ ላይ እንዳለው የሩጫው ‘የመጀመሪያ መስመር’ (start line) አለ አይደል፣ እሱ መስመር ላይ አሮጌው አመት የሚል ይፃፍበታል ከዛ ‘የመጨረሻው መስመር’ (finishing line) ላይ ደግሞ አዲሱ አመት የሚል ይፃፍበትና ‘ፕሬዝዳንት’ ሀይሌ ገብረስላሴ ከመጀመሪያው መስመር ተነስቶ ወደ መጨረሻው መስመር በመሮጥ ሪቫኑን ይበጥሰውና፣ በኩራት… የባንዲራ ዘንግ በአፉ ሳይሆን በእጁ ይዞ… "እንኳን ከአሬጌው አመት ወደ አዲሱ አመት በሩጫ አደረሳችሁ!" ይለናል ማለት ነው…
ሌላው ደግሞ… የሆነ የቦኖ ውሃ ወይም የአዲስ ትምህርት ቤት ምረቃ ላይ ሀይሌ ሪቫን እንዲቆርጥ መቀስ ሲሰጠው ያው እንደለመደው መቀሱን ጥሎ እየሮጠ ሄዶ ሪቫኑን በደረቱ ይበጥሰዋላ… ከዛ ስፖርት-ኮላ አሁን ገበያ ላይ ስለሌለ ኮካ-ኮላ በአንድ ትንፋሹ ይጨልጥና… እምምምም…. "ኢ-ት-ዮ-ጲ-ያ!" ይላል… (ኮካ-ኮላዎች፣ በዚህ አጋጣሚ ለማስታወቂያዋ ሰሞኑን ቢሯችሁ እመጣለው)
በቃ ምንአለፋችሁ… በአጭሩ… ኢንቨስተር፣ ሯጭ፣ አዝናኝ፣ የአገር ሽማግሌ… ሌላም ሌላም… የሆነ ፕሬዝዳንት ሊኖረን ነው… አልቸኮላችሁም? ቀላል ቸኩያለው!
ቆይ ግን ሀይሌ ፕሬዝዳንት ሲሆን ሱፍ ነው ወይስ የብሄራዊ ቡድኑን ቱታ የሚለብሰው? መቼም ሱፍ ከለበሰ አዲዳሶች (adidas Company) የሚቀየሙት ይመስለኛል… ያለበለዚያ ግን አዲዳሶች እራሳቸው ሱፍ ማምረት ሊጀምሩ ነው ማለት ነው… እርግጠኛ ነኝ ደግሞ እንደሚያደርጉት… ምክንያቱም እንኳንስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ቀርቶ ድሮም ሀይሌያችን አለም አቀፍ ተፅኖ ፈጣሪ ነዋ!
እኔ እምለው… ሀይሌ ፕሬዝዳንት ሲሆን መሮጥ ያቆማል ማለት ነው? ቢያንስ በአለም አቀፍ ደረጃ እንኳን ባይወዳደር ታለቁ ሩጫ ላይ አይሮጥም? እንደኔ እንደኔ ግን በአለም አቀፍ መድረክ ቢያንስ አንዴ ሮጦ ‘ባለ ወርቅ መዳሊያው ፕሬዝዳንት’ ተብሎ ጊነስ ላይ ስሙን ማስመዝገብ አለበት…
ከዛ ወደ ኢትዬጲያ መጥቶ አቀባበል ሲደረግለት ማሰብ ነው… ክቡር፣ አትሌት፣ ‘ፕሬዘዳንት’ ሀይሌ ገብረስላሴ በምክትል ፕሬዝዳንትና እንትን ሚኒስቴሩ በአቶ እገሌ የአበባ ጉንጉንና ይሄን ያህል ሄክታር መሬት ስጦታ በሽልማት መልክ ተበረከተላቸው ምና ምን አይነት ዜና እንሰማለን… አሁንም… እንደኔ እንደኔ ሀይሌ ቢያንስ የጊነስ ቡኩ ሪከርድ ቀርቶበት ለመሬቷ ሲል ቢሮጥ አሪፍ ነው… ምክንያቱም የመጨረሻው ነዋ የምትሆነው… ኋላ ፕሬዝዳንት ሲኮኑ ሀብት ማስመዝገብ ምና ምን የሚባል ነገር ስላለ ማለቴ ነው…
እርግጠኛ ነኝ ሀይሌ ፕሬዝዳንት ሲሆን የቱሪስቶች ቁጥር እንደሚያሻቅብ… በቃ አገራችን ከታሪካዊ መስህቦቿ ባሻገር አዝናኝ የቱሪስት መስህብ ልትሆን ነው… ከነ ሉሲ ይበልጥ ቤተ መንግስቱ በበርካታ ቱሪስቶች ሊጎበኝ ነው… (Run with the president) ‘ከፕሬዝዳንቱ ጋር ሩጥ’ የሚል ፕሮግራም እያዘጋጁ ይሄን ዶላር መሰብሰብ ነው…
ሌላው ስፖርት ኮሚሽኑን በሚኒስቴርነት ደረጃ እንዲቋቋምም ሎቢ ሊያደርግ ይችላል የሚል ግምት አለኝ… እናም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመታዊ የበጀት ድልድል ሲወጣ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለስፖርታዊ መሰረተ ልማቶች እንደሚመደብም ከወዲሁ መገመት አያዳግትም… ፓርላማው ባያፀድቀው እንኳን ሀይሌ ከግል አካውንቱ ፈሰስ ሊያደርግ ይችላል የሚል ግምት የለኝም… ምክንያቱም እሱ የቢዝነስ ሰው ነዋ! "ቀጥተኛ ትርፌ ምንድነው?" የሚል ጥያቄ መጠየቁ አይቀርም…
ዌል እንግዲክ… የዛሬውን ፖሊቴይመንቴን በዚሁ ላብቃ፤ ስለ ሀይሌ ፕሬዝዳንትነት ሳስብ የታዩኝ ጉዳዬች ለዛሬ እኒህ ናቸው፤ ሰንበት ብሎ አዳዲስ ሃሳብ ከመጣልኝ፤ እንደገና እመጣባችኋለው… ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!
.....................
በነገራችን ይህች ፅሁፍ በቀጣዩ ማክሰኞ በኢትዮ-ምኀዳር ላይ ትወጣለች፤ በዚህ አጋጣሚ ጋዜጣውን ገዝታችሁ ሌሎችንም አሪፍ፣ አሪፍ ፅሁፎች እንድታነቡ እጋብዛችኋለው…

Thursday, June 13, 2013
የወንደ-ላጤውና የሰራተኛዋ ‘ሜሞ’
ይህች ፅሁፍ በአንድ ወቅት በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት አብሮኝ ይሰራ ስለነበር ናሆም ስለሚባል ወንደ-ላጤና ስለሰራተኛው ገበያነሽ (ጋቢ) የምንጨዋወትባት አሪፍ ወግ ናት፤ ዘና በሉ…
ቅድመ-ወግ
ናሆም፡ እድሜው በሃያዎቹ አጋማሽ የሚገኝ ምርጥ ልጅ ነው፤ በቃ ሙድ የገባው፣ የአራዳ ልጅ የምትሉት አይነት… ተቆራርጣ የምትደርሰው የወር ደሞዙ ባለ አራት ዲጅት ልትሆን ትንሽ የቀራት… በዛችው ደሞዙ ቤት ተከራይቶ ተመላላሽ ሰራተኛ ቀጥሮ የሚኖር… ‘እቺን ደሞዝ በምን አይነት ብልሃት ነው የምታብቃቃት?' ሲባል ‘በአስማት' የሚል፣ ኑሮን ቀለል አድርጎ የሚኖር ምርጥ ልጅ…
ገበያነሽ፡ እንደ ናሆም ሁሉ ሙድ የገባት ስትሆን፤ ጎበዝ፣ የ10ኛ ክፍል የማታ ተማሪ ናት፡፡ ናሆምን ጨምሮ ወደ አምስት የሚደርሱ ወንደ-ላጤዎች ጋር በመስራት ራሷን የምታስተዳድር ሁለገብ ፍሪ-ላንሰርም ነች… ጋቢ በጠዋት ተነስታ የሁለት ወንደ-ላጤ ቤቶችን ስራ አቀለጣጥፋ ጨርሳ ናሆም ቤት ወደ አራት ሰዓት ገደማ ትደርሳለች፡፡ ናሆም ደግሞ ከእሁድ በስተቀር ከሁለት ሰዓት በፊት ከቤቱ ስለሚወጣ ከጋቢ ጋር የሚገናኙት በ‘ሜሞ' (አጭር የፅሁፍ ማስታወሻ) ነው፡፡
የናሆምና የጋቢ ሜሞዎች ትዕዛዝና መረጃ ከመለዋወጫነት በዘለለ ስለ ብዙ ጉዳዮች በስፋት የሚያወጉበት፣ የሚቀላለዱበት፣ የሚበሻሸቁበት፣ የሚደናነቁበት… ወዘተ ነው፡፡ እነዚህ ብጫቂ ወረቀቶች በሁለቱ መካከል ያለውን ንፁህ እህታዊና ወንድማዊ ግንኙነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ሲሆኑ፤ ስነፅሁፍዊ ይዘታቸውም የሚናቅ አይደለም፡፡ ሜሞዎቹን ሲያሻቸው በእንግሊዘኛ፣ አልያም በአራዳ ቋንቋ ስለሚፅፏቸው አንዳንድ ጊዜ ከፅሁፍ ይልቅ ወሬ ቢመስሉም ስርዓተ-ነጥብን ሳይቀር በአግባቡ ያካተቱና አንዱ ከሌላው በቀርፅም በይዘትም የማይገናኙ ናቸው፡፡ አስቂኝ ወሬ ወይም ተረባ በመሃከል ካለ የሳቅ ድምፃቸውን ሁሉ ሳያስቀሩ ያስገባሉ፤ ናሆም- ካካካካ… ጋቢ- ቂቂቂቂ… እያለች፡፡
ደስ ብሏቸው ይፃፃፋሉ… አንዱ የሌላውን ለማንበብ ይቸኩላል… እንኳን እነሱ እኛም ሳንቀር የቢሮ ስራችንን የምንጀምረው በእኒህ አዝናኝ ፅሁፎች ነበር፡፡ እንደውም፣ እነዚህን ፅሁፎች ማሳተም አለብህ እያልኩ እወተውተው ነበር፡፡ ወደፊት ‘የወንደ-ላጤውና የሰራተኛዋ ‘ሜሞ'' በሚል ርዕስ እንደሚያሳትማቸው ከልብ እየተመኘሁ ከሜሞዎቹ በጥቂቱ እነሆ… ኤን ቢ፡ ፅሁፎቹ እንደወረዱ የቀረቡ ናቸው…
ቀን፡ 10/4/2001ዓ.ም
ይድረስ፡ ለገበያነሽ (Arrive: for Marketing) ካካካካ…
ጋቢዬ፣ ዛሬ ጓደኛዬን እቤት ምሳ ስለጋበዝኩት ቤቷን ሰንደል ጨስ ጨስ አድርጊባትና አሪፍ ምሳ አዘጋጂልን፤ አራት ድንችና ሶስት ራስ ሽንኩርት አለ በሱ አሪፍ፣ ጣት የሚያስቆረጥም ጥብስ ፍርፍር ስሪልን… ካካካካ… ለማንኛውም ለእንጀራና ሌላ መግዛት የምትፈልጊው ነገር ካለ ብዬ ኮመዲኖው ላይ ሃያ አምስት ብር አስቀምጬልሻለሁ፡፡ መልስ ካለ እዛው አስቀምጪልኝ፤ በተረፈ መልካም ፈተና፡፡
ናሆም፣ ከማይነበብ ፊርማ ጋር
ቀን 10/4/2001ዓ.ም
ይድረስ፡ ለናሆም…
ኡኡቴ! አንተን ብሎ ምሳ ጋባዥ…ቂቂቂቂ… ለማንኛውም አራቱ ድንቾች ትንንሽ ስለሆኑ ግማሽ ኪሎ ድንች ገዝቻለው ከዛ ውጪ ቲማቲም፣ ሽንኩርትና እንጀራ ገዝቼ የተረፈውን 1ብር ከ50 ኮመዲኖው ላይ ላስቀምጠው ብዬ እናቴ ለታላቅ አይመለስም ትል የነበረው ትዝ ሲለኝ ይዤው ሄጃለሁ… ቂቂቂቂ… በተረፈ በአራት ድንችና በሶስት ሽንኩርት የሚሰራ ጥብስ ፍርፍር ስለማልችልበት አልጫ ድንች ወጥና… ጥብስ… አምሮህ እንዳይቀር ብዬ… ጥብስ ቅጠል ያለው ፍርፍር ሰርቼልሃለው... ቂቂቂቂ… ያው ወጡ ከቀዘቀዘባችሁ አሙቃችሁ ብሉ… ዘይት ስለጨረስኩ ለነገ ብር አስቀምጥልኝ፡፡
ቻው፣ ገበያነሽ
ቀን 11/4/2001ዓ.ም
ይድረስ ለጋቢያንስ
ኸረ ጋቢያችን! ጨዋታ ጨምረሽ የለ እንዴ! የትላንቱ ተረብሽን አልቻልኩትም፤ ልቤ እስኪፈርስ ነው ያሳቅሽኝ… ወጡም በጣም አሪፍ ነበር፤ እኔ እምልሽ፣ ቅቤ ደግሞ ከየት አምጥተሸ ነው? ከሼባው ወንደላጤ ቤት ቋ አድርገሽ እንዳይሆን? ቤተሰብ አደረግሽን እኮ…ካካካካ… በነገራችን ላይ፣ ቤት ውስጥ ምንም አስቤዛ በሌለበት ምግብ የምትፈጥሪው ነገር ብዙም አይገባኝም፤ ለነገሩ እንዲገባኝም አልፈልግም፣ በአስማትም ይሁን በፀሎት ዋናው ቁም ነገር የሚበላ ነገር መኖሩ ነው፡፡ የትም ፍጪው… (Where crash bring my ash) አይደል የሚባለው…ካካካካ… መቼም ባንቺ መላ ባይሆን ኖሮ ይቺ ደሞዜ ሁለት ሳምንት እንኳን በቅጡ እንደማታዘልቀኝ ታውቂዋለሽ፡፡ ለማንኛውም በድጋሚ አመሰግናለሁ፣ የኔ አስማተኛ… ካካካካ… የዘይት ብር ኮመዲኖው ላይ አስቀምጬልሻለሁ፡፡
ፒስ በይ- ናሆም
ቀን 11/4/2001ዓ.ም
ለ፡ እርሶ
አንተ ነገረኛ! እንደው ምን ይሻልሃል… ለማንኛውም ወጡ ቅቤ አለው ምናምን ያልከውን ወሬ ቅቤ ያለው እስኪመስል ይጣፍጣል ለማለት ከሆነ ከአንገቴ ሰበር፣ ከወገቤ ጎንበስ ብዬ ተቀብዬዋለሁ …ይህቺ የፈጠርካት ታሪክ ግን ብዙም አልተመቸችኝም፤ እኔኮ ፕሮፌሽናል ነኝ! እንዴት ከአንዱ ቤት ወስጄ ለሌላው እሰራለሁ፣ ከአስራ ሁለቱ የስነምግባር መርሆች መካከል አንዱ ታማኝነት እንደሆነ ረሳኸው? ቂቂቂቂ… ለማንኛውም ሀሳብህን በመርህ ደረጃ ተቀብዬዋለው ባይሆን ሚስጥሩን ልንገርህ፣ አንዳንድ ጊዜ ምንም አስቤዛ ሳይኖር ምግብ የምሰራልህ ከራሴ ቤት እያመጣሁ ነው፤ ምክንያቱም ስለምታሳዝነኝና ስለምታዝናናኝ… በዛ ላይ ልክ እንደ ወንድሜ ስለማይህ ነው፡፡ በል አሪፍ ምስር ወጥ ሰርቼልሃለው አሙቀህ ብላ… ያጠብኳቸውን ልብሶች አልጋው ላይ አጣጥፌ አስቀምጬልሃለው… ብር ስላልነበረኝ እንጀራ አልገዛውልህም፡፡
እደር፣ ጋቢ
ይህች ቀጣይዋን ሜሞ ናሆም በጋቢ የምግብ ዘይት አጠቃቀም በጣም ቅር በመሰኘቱ የፃፋት ናት፡፡ ለአንድ ወር የሚገዛትን አንድ ሊትር ከግማሽ ዘይት እሷ በሁለት ሳምንት ጭጭ ስለምታደርጋት እንዲህ ሲል ፅፎላታል…
ጋቢ ከተጫዋችነቷና ከምስኪንነቷ ባሻገር የዋህ ቢጢ ናት፤ የነገሯትን ሁሉ አምና የምትቀበል… ከቅርበታቸው የተነሳ ስለ ዘይቱ የፃፈውን ሜሞ አንብባ ‘በግልፅ ዘይቴን አትጨርሺ አትልም…' ብላ ኩም የምታደርገው መስሎት ነበር፤ ነገር ግን ልጅቷ ጋቢ ናት… አምና ተቀብላዋለች፡፡
ለተከበሩ…
ጋቢሽካ፣ የትላንቱ ምስር ወጥ በጣም አሪፍ ነበር፤ ነገር ግን ቅባት በጣም ስለበዛበት ነው መሰለኝ ጨጋራዬ ሲነድ ነው የዋለው፡፡ ሌላ ነገር ይሆናል እንዳልል ውጪ አልመገብም፤ ባለፈው ሳምንትም የሰራሽልኝን ድንች ወጥ ቅባቱን እየፈራሁ በልቼው በቃ ምን አለፋሽ፣ አንቆራጠጠኝ… ስቃጠል ነው የዋልኩት… ለማንኛውም ካሁን በኋላ የምትሰሪልኝ ወጦች ላይ ዘይት በጣም አትጠቀሚ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ የልብ በሽታ እንዳለብኝ ነገሬሻለሁ አይደል? በዘር ነው መሰለኝ እኛ ቤት ሁሉም የልብ በሽታ ታማሚ ስለሆነ ለዘይት የሚደረገው ጥንቃቄ ለየት ያለ ነው፡፡ ሰሞኑን ደረጃ ስወጣ ሁሉ ልቤ ድው ድው እያለች ነው፡፡ እናም… ባጭሩ… እንዳልጭርብሽ ለማለት ያህል ነው! ካካካካ… በነገራችን ላይ ሶስቱንም የፊዚክስ ጥያቄዎች በትክክል ሰርተሻቸዋል፤ የሆነ የተሳሳትሽው ስቴፕ ነበረ እሱን ምልክት አድርጌበታለሁ በደንብ እይው፡፡
ቻው! ናሆም
ለ፡እርሶነቶ…
ናሆሜ ለምንድን ነው እስከ ዛሬ ድረስ ያልነገርከኝ! እኔ እኮ ላንተ ማሰቤ ነበር፤ ጣፍጦህ እንድትበላ ብዬ ነው ቅባት የማበዛው፡፡ ለማንኛውም ከአሁን በኋላ አስተካክላለሁ፡፡ አይዞህ! አትጭርም… ቂቂቂቂ.. ለልብ በሽታህ ደግሞ ጠዋት ጠዋት ትንሽ ዱብ ዱብ በልባት… ሰሞኑን ብር ሳታስቀምጥልኝ እየወጣህ ስለሆነ ምንም ነገር አልገዛሁልህም፤ ሽሮም የመጨረሻዋን ዱቄት አራግፌ ነው የሰራሁልህ… ለነገ ምን እንደምሰራልህ አሳውቀኝ…
ደህና እደር፣ ጋቢ
በነገራችን ላይ ምንም እንኳን በመሃከላቸው ጥሩ ቅርርብና ግልፅነት ቢኖርም የዘይት ቅነሳውን እውነተኛ ምክንያት ለምን እንዳልነገራት ናሆምን ስጠይቀው እንዲህ ነበር ያለኝ... ‘ባክህ! እሷ ምስኪን ስለሆነች እንደዛ ካልኳት ዘይት ከራሷ ቤት እያመጣች ልትሰራልኝ ትችላለች፤ ያን ደግሞ እኔ አልፈልኩም…’ የናሆምና የጋቢ መተሳሰብና መዋደድ በጣም የሚያስቀና፣ የሚያዝናና… ብዙ ብዙ የሚባልለት ነው…
እስኪ በመጨረሻ ጋቢ ከላይ ለፃፈችው ሜሞ ናሆም የፃፈላትን መልስ አስነብቤያችሁ ወጌን ላብቃ…
ለ፡ ጋቢሻ...
ጋቢቾ! ፒስ ነው አይደል? ጠፋህ ነው ያልሽው? አንቺ ምን አለብሽ… አምስት ደሞዝ እየበላሽ… ካካካካ… ለማንኛውም የጠፋሁት… ያው እንደምታውቂው አራተኛው ሳምንት አይደል፤ እናም ብር ኔፕ ሆኜ ነው… ለአስቤዛ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ስሌለኝ ለእራት የሆነች ነገር ይዤ እገባለሁ፡፡ ባይሆን ‘ምን ሰርቼ ልሂድ?' ላልሽው፣ ምንም ሳትሰሪ ከምትመለሺ ፑሻፕ ሰርተሽ ሂጂ… የቻልሽውን ያህል… ካካካካ… ሰራሁልሽ… ካካካካ...
ናሆም፣ ቻው!

የድብርታሙ ሰው ዲያሪ
ቀን፡ ግንቦት 12 13
12… ኤጭ!
ዛሬ
ቀን ስንት ነው? እኔ እንጃ! ለነገሩ ስንትስ ቢሆን ምን አገባኝ፣ ምን ልዩነት ያመጣል… የቀን ማስታወስ ችግሬ እንዳለ ሆኖ ሃያ
ምናምን አመት የኖርኩ ይመስለኛል፡፡ እድሜዬን በሙሉ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ… እያልኩ ስቆጥር፤ ህይወቴን በሙሉ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ እሮብን…
ስደጋግም ኖሬያለሁ ግን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ ቢያንስ የቀናቱ ስም እንኳን አልተቀየረም፣ የወራቱ ስም እንኳን አልተቀየረም፤
ሲደብር! ለነገሩ ህይወት ማለት አሰልቺ የሰባት ቀናት ሳምንት እንዲሁም ተደጋጋሚ የአስራ ሁለት ወራት አመት ነች (ኦ! ለካስ አስራ
ሶስት ወራት ናቸው ያሉን፣ ድንቄም!)
…ጠዋት፣
ከሰዓት፣ ማታ፣ ቀን፣ ሌሊት… እስቲ አሁን የህይወት አጓጊነትዋና ጣዕሟ የቱ ጋር ነው? ኑሯችን በነዚህ ደባሪና አሰልቺ አዙሪት
ውስጥ የተዘፈቀች አይደለችምን? ለምድን ነው አራሳችንን የምናታልለው፣ ለምንድን ነው "እያንዳንዷ ቀን አዲስ ናት"
እያለን የምንፎጋገረው? እውን እያንዳንዱ ቀን አዲስ ነው? ነው!? ከሆነስ ምኑ ጋር ነው አዲስነቱ? በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መብላት፣
መውጣት፣ መግባት፣ መተኛት፣ መነሳት፣ እንደገና መተኛት፣ እንደገና መነሳት… ኡፍፍፍ.. ደባሪ!
ቀን፡ ግንቦት 13 14… አጭ!
በቃ በንጋታው
ቅዳሜ/የእረፍት
ቀን… ቀኑ እንደተለመደው ነው… ደባሪ! አልጋዬ ውስጥ ስንከባለል ቆይቼ ረፋድ ላይ በግድ ተነሳሁ፤ የምግብ ፍላጎቴ ጠፍቷል ነገር ግን እንደምንም ብዬ ቤት ውስጥ የነበረ ምግብ በግድ ቀማመስኩ፡፡ ቀጥሎም ምን ማድረግ
እንዳለብኝ ወይም የት መሄድ እንዳለብኝ ማሰላሰል፣ ማውጠንጠን ጀመርኩ፡፡
ጓደኞቼ
ጋር ልሂድ፣ ፊልም ልይ፣ ወይስ እዚው ቁጭ ብዬ አዲስ የገዛኋትን መፅሃፍ ላንብብ… አስራ ሁለት ልብ ሆንኩ፤ በመጨረሻም ረጅም ደቂቃዎችን
ከፈጀ ውስጣዊ-ግለ-ጭውውት (Internal Monologue) በኋላ፣ አውጥቼ አውርጄ ማለቴ ነው ቤቴ ቁጭ ብዬ መፅሃፌን ለማንበብ
ወሰንኩ፡፡ በነገራችን ላይ ሰው ማግኘት ሲደብረኝ ወይም ወደ ውጪ መውጣት ሲያስጠላኝ ሁሌም የማደርገው ይህንን ነው፤ ማንበብ፡፡
መፅሃፍትን የማነበው ህይወቴን ለመርሳት ነው፤ እራሴን ለመርሳት፤ ‘ስለ እውነተኛው’ አለም (ስለ ‘ገሃዱ አለም’) ላለማሰብ፡፡
የፍልስፍና
መፅሃፍቶችን ማንበብ የምመርጠውም ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ መፅሃፍት በአብዛኛው የ‘ገሃዱ አለም’ ቀጥተኛ ነፀብራቆች አይደሉምና፡፡
እኔ ለምኖረው አይነት ህይወትና ለጥያቄዎቼ መልስ የሚሰጡኝ እንዲህ ያሉ መፃህፍት ብቻ ናቸው፡፡ ብዙ የPhilosophical Skepticism
(ነቀፌታዊ ወይም ጥርጣሬያዊ ፍልስፍና) መፃህፍትን አንብብዬለው፡፡
በውሳኔዬ
መሰረት መፅሃፌን ካስቀመጥኩበት መደርደሪያ ውስጥ አውጥቼ ለማንበብ በመስኮቴ ፊት ለፊት በተቀመጠው ፎቴ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ(ዘፍ
አልኩ)፡፡ ወዲያውም አንዴ ከተቀመጥኩ መነሳት ያለመውደድ ስንፍናዬ ትዝ አለኝና በቅርብ የሚያስፈልጉኝን እቃዎች በእጄ እርቀት እንዲሆኑ
አድርጌ አቀራረብኩ፤ ሲጋራ፣ የሲጋራ መለኮሻ፣ መተርኮሻ፣ አንድ ሁለት ቢራዎች፣ የሲዲ ማጫወቻ የርቀት መቆጣጠሪያ፣ ‘ቢራ መክፈቻ’
(ለስላሳ ስለማልወድ እናንተ ‘ለስላሳ መክፈቻ’ የምትሉትን እኔ ቢራ መክፈቻ ነው የምለው)
ሶፋዬ
ላይ ጀርባዬን አደላድዬ ቢራዬን ከፍቼ ጎርጎጭ ካደረኩ በኋላ ሲጋራዬን ለኮስኩ፣ ጭሱን ወደ ውስጥ በስስት ምጥጥ አድርጌ በአፍንጫዬ
በኩል ወደ ውጭ በማስወጣት ጠባቧን ክፍሌን በጭስ ሞላኋት፡፡ አሁን ለማንበብ ዝግጁ ነበርኩ፤ ‘ያልተሄደበት መንገድ’
ትላለች የመፅሃፏ ርዕስ፤ የመፅሃፉ
የውጭ ሽፋን ላይ ለአፍታ አፈጠጥኩ ሁለት ቅያሶች ያሉት መንገድ ይታያል፣ በዙ ሰዎች በአንደኛው መንገድ ላይ ተሰልፈው ይታያሉ፤
በሌላኛው መንገድ መጀመሪያ ላይ ደግሞ እነዚያን የተሰለፉትን ሰዎች ቆሞ የሚያይ ሰው ይታያል፡፡
ወደ
ውስጥ ገፅ ዘለቅኩ፣ ገፅ-3፣ መታሰቢያ፣ “ይህ መፅሃፍ ላንተ ነው!” “ለኔ!?” አልኩ ሳላስበው፤ ፅሁፉን እኔው እራሴው ያነበብኩት
አልመሰለኝም ይልቁንም ጎርነን ያለ ድምፅ ያለው ሰው ያነበበልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ …የመፅሃፉን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማንበብ
ጀመርኩ፤ የቃላቶቹ ጥፍጠትና ጥንካሬ ደስ ይላል፤ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ከመግባቴ በፊት ቢራዬን ጎንጨት አልኩኝ፤ ንባቤ ቀጥሏል፣
አንድ አንቀፅ ላይ ግን ቀልቤ አርፏል ደጋግሜ አነበብኩት ወደ ቀጣዩ አንቀፅ ማለፍ አልቻልኩም፡፡
“…
ህይወት ሙከራ ናት፤ አዎ! የሙከራ ፈተና! ህይወት የእውነት ብትሆን
ኖሮ የት መሄድ፣ መቼ፣ ምን፣ ለምን፣ ማድረግ እንዳለብህ ይነገርህ ነበር…” እውነትም! አልኩ ውስጤ ላለው የ‘ገሃዱ አለም’
አውነተኝነት ጥርጣሬና ነቀፌታ ምላሽ ያገኘው መሰለኝ፤ ደስ አለኝ! ለሰው ልጅ ያሰበው ወይም የተናገረው ነገር ልክ ሆኖ እንደማየት
የሚያስደስተው ነገር ያለ አይመስለኝም፤ አላልኩህም/ሽም! ለማለት፡፡ በተመሳሳይ ስሜት እኔንም በጣም ደስ አለኝ፡፡
ንባቤን
ቀጠልኩ “…ህይወት በተከታታይ ፈተናዎች የተሞላች ናት፣ ተፈትነህ ትወድቃለህ፣
እንደገና ታጠናና ታልፋለህ፣ ከውድቀትህ ትነሳለህ፣ ደረጃህ ከፍ እያለ በመጣ ቁጥር በሌላ ፈተና ትወድቃለህ፣ አሁንም ከውድቀትህ
ትማርና አሻሽለህ ታልፋለህ… ይህ የማይቀር መንገድ ነው፤ የማይቀር የህይወት ጉዞ፡፡ ታዲያ የዚህ ጉዞ አጓጊነትና ጣፋጭነት የሚወሰነው
በምትመርጠው መንገድ ነው፤ የትኛውን መንገድ ነው የመረጥከው? ብዙሃኑ የሄደበትና የተሰለፈበትን ወይስ ሌላው ልብ ያላለውን፣ ያልተሄደበትን
መንገድ? የህይወት ጣዕሟና አጓጊነቷ እዚህ ላይ ነው እያንዳንዱ መንገድ የራሱ የሆነ መልስና ውጤት አለው፡፡ ተነሳ! ውጣ! ሂድ!
ህይወትህን ሞክራት! ፈተናውን ስትሞክር ለመሳትፍ ሳይሆን ለማለፍ፣ ለመብለጥ ሳይሆን፣ ለመላቅ ይሁን፤ ያልተሄደበትን መንገድ ሞክር!
ምናልባትም ታዕምር ታገኝ ይሆናል፣ ማን ያውቃል ታሪክ ትሰራ ይሆናል… ማን ያውቃል! ለነገሩስ ህይወት ሙከራ አይደለችምን? ”
ጀምበር
እያዘቀዘቀች ነው፤ አይኖቼን ከመፅሃፉ ላይ መንቀል አቃተኝ፤ ለአፍታ እንኳን፤ ቀልቤን ገዝቶታል፣ ውስጤ ገብቷል፣ ፊደል በፊደል፣
ቃል በቃል እየለቀምኩ ነው የማነበው፤ በሚገባኝ ቃላት፣ በምረዳው አገላለፅ ለእኔ የተፃፈልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ በቃላት ጠግባችሁ
ታውቃላችሁ? አንድ ነገር ከመጠን ሲያልፍ እንደሚያቅለሸልሸው ነው የሆነብኝ፣ የሆነ የማስታወክ ስሜት ተሰማኝ፣ በቃላት ቁንጣን ተወጠርኩ፣
የፊደላት ህቅታ፣ ወደ ላይ ሊለኝ ሆነ… እንደ ምንም ብዬ መፅሃፉን ከአይኔ ላይ መነጨኩት፡፡
ሲጋራዬን
ለኩሼ በረጅሙ ወደ ውስጥ ከመጠመጥኩት በኃላ ኡፍፍፍፍፍ! ብዬ
በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡ ከዛም የመፃፍቱን ቃላቶች በተመስጦ ማውጠንጠን ጀመርኩ፡፡ በቃላቶቹ ያ ጎርናና ድምፅ ያለው ሰውዬ እየደጋገመ
የሚገስፀኝ መሰለኝ፣ በሚቆጣ ትዕዛዛዊ ድምፅ፡፡ ማንነቴን ወደ ኋላ ዞር ብዬ መገርመም ጀመርኩ፣ በሂሳዊ አይን፡፡ “ህይወቴን በጥርጣሬና
በነቀፌታ ሞልቻት ኖሬያለሁ፤ በዚህም ምክንያት ችሎታዬንና አውቀቴን አውጥቼ እንዳልጠቀም ሆኛለው፣ እውቀቴ የመመፃደቅና የትችት ነበር፤
በራሴ ድብርታም አለም ውስጥ ስሽከረከር ጊዜዬን ፈጅቼዋለሁ… እራሴን
ጠዘጠዝኩት፤ አቤት ግለ-ሂስ!”
ውስጤ
ሲታደስ ተሰማኝ፤ በሀሴት ተሞላሁ፡፡ “…ምናልባትም ህይወት እኔ እንደማስባት ጨለማ ላትሆን ትችላለች፣ ምናልባትም ብሩህ መንገድ
ይኖራታል፤ እይታዬን የማስተካከያ ጊዜዬ አሁን ነው…” አልኩኝ፣ ለራሴ ይሁን ለባለ ጎርናናው ድምፅ ሰውዬ ሳላውቀው፡፡
ወደ
ውጪ መውጣት ፈለ’ኩ፣ የህይወትን ሌላ ጎን ለማየት ጓጓሁ፣ ባልተሄደበት መንገድ ለመሄድ ፈለኩ፤ ዳሩ ምን ዋጋ አለው ቀኑ አርጅቶ
ነበር፤ ምሽት፡፡
ግንቦት 14 (ለመጀመሪያ ጊዜ ሳልሰርዝ ሳልደልዝ ቀን የፃፍኩበት ቀን)
አይናችሁን
መጀመሪያ ገልፃችሁ ነው ከዛ የምትነቁት ወይስ ነቅታችሁ ነው አይናችሁን የምትገልፁት? እኔ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቴ በፈገግታ በርቶ
ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ አይኔን ገለፅኩ፤ ነቃሁ! በሬን ከፍቼ እስክወጣ አላስችል አለኝ፣ ባልተሄደበት መንገድ ጉዞዬን ለመጀመር አሀዱ
አልኩ፤ ደስ ሲል!
ይድረስ ለውዷ እናቴ፣ ሉሲይድረስ ለውዷ እናቴ፣ ሉሲ
መቼም ለዘንድሮ የትንሳኤ በዓል ወደ አገሩ ያልተከተተ ኢትዮጲያዊ የለም፡፡ ያው ከአገሩ የወጣ ሰው ወደ ትውልድ ቀዬው ለመመለስ ምክንያት መደርደሩ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ታዲያ ለእንዲህ አይነቱ ሰው በተለይ ለክርስቲያኑ ማህበረሰብ ወደ አገሩ ለመመለስ እንደ ፋሲካ ያለ ድንቅ በዓል አይገኝም፡፡ ይሄ በውጪ ያሉ ሰዎች ይናፍቀናል የሚሉት የዓውድ-ዓመት ሽታና ግርግር ከሌሎች በዓላት በተሻለ ሁኔታ በትንሳኤ በዓል ስለሚደምቅ ነዋ፡፡
ታዲያ
በዚህ የትንሳኤ በዓል በህይወት ያለ ኢትዮጲያዊ ቀርቶ አንቺ ውዷ እናታችን-ሉሲ እንኳን ከአምስት አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ
ወደ አገሽ ከተፍ ማለትሽን ሰማን፡፡ ፋሲካን ከዘመድ አዝማዶቼ፣ እትብቴ ከተቀበረባት፣ አፅሜ ተቆፍሮ ከወጣበት የትውልድ አገሬ ልከተት
ብለሽ፡፡ ለማንኛውም እንኳን በሰላም ወደ አገርሽ ተመለሽ ብለናል፡፡ እንኳን በሰላምና በጤና ላገርሽ፣ ለአፈርሽ፣ ለቀዬሽ አበቃሽ ብለናል፡፡ ድንቅ ነሽና ድንቅ የሆነ የዳግማ-ትንሳኤ በዓልንም ተመኝተናል፡፡
ከሁሉ
ከሁሉ የደነቀኝ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? ስለ አንቺ የሚወራው አሉባልታ መብዛቱ ነው፤ እንደውም ምን ሲሉ ሰማሁ መሰለሽ፣ ሉሲ
አሜሪካን አገር በነበራት ቆይታ በቁሙ ያለ ኢትዮጲያዊ ያልሸቀለውን ዶላር ሸቃቅላ ነው የመጣችው እያሉ ሲያወሩ፡፡ እሰይ! እንኳን!
ደግ አደረግሽ! እንደ አንዳንድ ዓላማ ቢስ፣ ቡኩን፣ ስደተኛ በብልጭልጭ ነገር ሳትታለይ፣ በዘመነው የውጭ አገር አኗኗር ሳትደለይ፣
የተሰደደሽበትን አላማ ሳትረሺ፣ አልበላም አልጠጣም ብለሽ፣ የሰራሻትን እያንዳንዷን ሽርፍራፊ ሳንቲም ሳትቀር በመሃረብሽ ቋጥረሽ
ወደ አገርሽ መመለስሽ ብልጥነት እንጂ ፋራነት አይደለም፡፡
ሌላ
ደግሞ ምን እያሉ ሲያወሩ ሰማሁ መሰለሽ፣ ሉሲ አሜሪካን አገር በሸቀለችው ዶላር ለእናቷ ሲኤምሲ አካባቢ ምን የመሰለ ቤት ገዝታላቸዋለች፣
ለአባቷ ደግሞ ሲኖ ትራክ፣ ለወንድሞቿ ለአንዱ ላዳ፣ ለአንዱ ሚኒ ባስ… ምናምን እያለ ሰዉ ያወራል፡፡ እውነት ይሆን ሉሲ?
የሚወራው
ነገር እውነት ቢሆንም እንኳን ምንም አይደለም ሉሲዬ፡፡ በሰው አገር ላብሽን አንጠፍጥፈሽ፣ የስንቱን አይንና ግልምጫ ችላ ብለሽ፣
በስንቱ ታይተሸ፣ ያገኘሽውን ገንዘብ ለራስሽ አንድም ነገር ሳታደርጊበት፣ መዘነጥ፣ መሽቀርቀር፣ ዳንኪራ መርገጥ አማረኝ ሳትይ ወደ
አገርሽ ይዘሽ መመለስሽ የሚያስመሰግንሽ እንጂ የሚያሳማሽ አይደለም፡፡ ይልቁንም የጀግና፣ የኩሩ ኢትዮጲያዊ ተግባር ነው፡፡ ኩሩ
የናቷ ልጅ! ልጅ ማለት እንዲህ ነው! የሚያስብልሽ ነው፡፡ አንዳንዱ በቁሙ ቤተሰብ ያሳዝናል፣ አገር ያሰድባል፤ እንደ አንቺ አይነቱ
ግን 'አይ ልጅ!' እየተባለ ይሞካሻል፡፡ ይኸው በሙትሽ እንኳን እኛ ጋር ነይ፣ እኛ እንይሽ እየተባለሽ በየቦታው፣ በየአገሩ ጥሪ
ይቀርብልሻል፤ ለእይታ ብቻ በርካታ ዶላር ይዘንብልሻል፡፡
በኔ
በኩል ወደ አገርሽ መመለስሽን ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? በቃ ይሄ በየቦታው ቁጭ ብሎ ወሬውንና
ሃሜቱን ከመሰለቅ ውጪ ቁም ነገር የማያውቀውን፣ የኩታራ አሉባልታና እነቶ ፈንቶ ወሬ ኩሽ አደርገሽዋ፡፡
አንድ
ሰሞን የእናትነት መንፈስሽ ካለሽበት ጠርቶኝ ነው መሰል በናፍቆት ተቃጥዬ "አረ የሉሲ ነገር እንዴት ነው፣ ጠፋችብን እኮ
ቤቷ ስንሄድ የምናገኘው ምስለ-አካሏ የሷነቷን ያህል መንፈስ የለውም፣ የእናትነት ጠረን የለውም፣ የእምዬን ናፍቆትና ርሃብ አያስታግስም"
ብዬ ብጠይቅ "አልሰሜን ግባ በለው! ሉሲ እኮ አሜሪካ ጥገኝነት
ጠይቃለች፤ ላትመለስ ነው የሄደችው አሉኝ" ጠላትሽ ክው ይበል፤ ክው ብዬ ቀረሁ፤ በድንጋጤ
እንዳንቺው አፅም ሆንኩልሽ፡፡ ጠላትሽ አመዱ ቡን ይበልና አመዴ ቡን አለ፡፡ አሁን ግን በቃ መምጣትሽን ስሰማ አንጀቴ
ቅቤ ጠጣ፣ የደስታና የናፍቆት ሲቃ ተናነቀኝ፤ ለነገሩ ያው የልጅ ነገር ሆኖብኝ ደነገጥኩ እንጂ ጨቅነሽ እንደማትጨክኚ፣ ቀርተሸ
እንደማትቀሪ ልቤ ያውቀው ነበር፤ ለማንኛውም በድጋሚ እንኳን በሰላም መጣሽልኝ እናቴ፡፡
ያው
የዚህ አገር ኑሮ እንደምታውቂው ነው፤ መቼም ትረሺዋለሽ ብዬ አላስብም፤ ምንም እዛ ብትሆኚም
ልብሽ እዚህ ነውና፡፡ ኸረ ለመሆኑ! ረስቼው ሳልጠይቅሽ፣ የዛሬ አምስት አመት ጥለሻት የሄድሻት አገርሽን እንዴት አገኘሻት? ፐ!
ጉድ ሆናለች አይደል! አዲስ አበባንማ ተያት በቃ ቀውጢ እኮ ነው የሆነችው፤ የሆነ የልማት አርበኛ ገበሬ የቆፈራት ትልቅ ማሳ እኮ
ነው የምትመስለው፡፡ ብቻ የሁን መቼም የአስፋልቶቻችን ማማርና መስፋት እራሱ ቀላል ነገር አይደለም ቢያንስ ቢርበን እንኳን ጥሩ
አስፋልት ላይ ተሰጥተን ጥርሳችንን እንፍቃለን፣ ሆዳችንን ረሃብ እየፋቀውም ቢሆን፡፡ በዛ ላይ ደግሞ እንደ 77ቱ ምናምና ይሄ ለፎቶ
የሚደብር ባግራውንድ አይኖረንም፤ በቃ… አለ አይደል… ቀብረር ያለ አስፋልት ላይ ባንቺ መሪነት ምርጥ የአፅም ሾው እናሳያለን፤
ልክ እንደ ማይክል ጃክሰን ክሊፕ፡፡
ኪ.ኪ.ኪ.ኪ.ኪ.… አልሽ? አይይይ…እ…
አንቺ ምን አለብሽ እናቴ፣ ሳቂ በድድሽ፣ ሆድ የለሽ፣ ጥርስ የለሽ እኛው እንደፈረደብን እናማር እንጂ፤ የፈለገስ ቢሆን ደግሞ እድሜ
ለአሜሪካን ዶላር፣ መመንዘር ነው፡፡ አይ የኔ ነገር፣ ይቅርታ የኔ እናት፣ ይሄ የኑሮ ነገር ሲነሳ ፀባዬ ሁሉ ቅይርይር ይላል ታውቂው
የለ ክፋት እንደሌለብኝ፤ መቼም አትቀየሚኝም፤ ደግሞ መቀየም እኮ የኢትዮጲያዊ ብቸኛ ባህሪ ነው፤ አንቺ ደግሞ አምስት አመት አሜሪካ
ተቀምጠሸ መቀየም የሚባለውን ቃል ከነመፈጠሩም የረሳሽው ይመስለኛል፡፡
እ…ሺ...! ታዲያ አሜሪካንን
እንዴት አገኝሻት? መቼም እንደነ እገሌ ምነው አሜሪካዊ በሆንኩ ብለሽ አልተመኘሽም፤ እንደውም እንኳንም ኢትዮጲያዊ ሆንኩ ነው ያልሽው
አሉ፡፡ ምክንያቱም አሜሪካዊ ብትሆኝ ኖሮ ማን ቆፍሮ ያወጣሽ ነበር፤ አሜሪካ ውስጥ አርኪዮሎጂስቶች ቆፍረው ሊያወጡት የሚችሉት እድሜ
ጠገብ ታሪካዊ ቅርስ ቢኖር የክርስቶፎር ኮሎምበስ የውሃ መያዣ ኮዳ ነዋ፤ በቃ ከዛ የዘለለ ታሪክ የላትማ፡፡ ታዲያ ኢትዮጲያዊ በመሆነሽ
ከነድህነታችንም ቢሆን አልኮራሽም? እንደውም ስሰማ፣ ፕራውድ ቱ ቢ ኢትዮጲያን የሚል ቲ-ሸርት አድርገሽ ሁላ ነው ወደ ኢትዮጲያ
የገባሽው ይባላል፤ እውነት ነው?
በነገራችን ላይ፣ ያው የደሃ ነገር ታውቂዋለሽ፣ አይሞላለትም፤ ላይ ታች ስል፣ ከዛሬ
ነገ እህዳለሁ ስል፣ መጥቼ ሳላይሽ ይኸው ዳግማ-ትንሳኤ መጣ፡፡ ቢሆንም ግን ይህቺ ደብዳቤ ከእኔ ቀድማ እንደምትደርስሽ አስባለሁ፡፡
በአካል ተገናኝተን የልብ የልባችንን እስክናወጋ፣ የፈረንጅ አገር ትዝብትሽንና ቆይታሽን እስክታጫውቺኝ፣ የናፍቆቴን ያህል ይህችን
እጥር ምጥን ያለች ደብዳቤ አሰናድቻለሁ፡፡
እስቲ
አሁን ደግሞ፣ ልጅ ነኝና እንደ ልጅ የልጅ ጥያቄ ልጠይቅሽ፣ ከውጪ አገር ምን አምጥተሸልኝ ይሆን? ላፕ ቶፕ፣ አይ ፎን፣ ስኒከር
ወይስ ቲሸርት? መቼም ቲ-ሸርትም እንኳን ቢሆን እንደ እነ እገሌ አይ ላቭ ኒው ዮርክ የሚል ቲሸርት አታመጪልኝም፤ ምክንያቱም አይ
ላቭ ኢትዮጲያ ብለሽ ነዋ የመጣሽው፡፡ ለማንኛውም ቸኮሌትም ቢሆን ይቀመጥልኝ ከሰሞኑ መጥቼ ሳላይሽ አልቀርም፡፡
"አይት በይ ነብሴ!"
(ይቺ ከፊል እንግሊዘኛ፣ ከፊል አማርኛ፣ ከፊል አማርዝኝ የሆነች ሀረግ፣ በእንግሊዘኛ Alright then፣ እንደማለት፤ አሜሪካ
ደርሰው የተመለሱ ጀለሶቻችን የሚያዘወትሯት ናት) አንቺም ሳትለምጂያት አትቀሪም ብዬ ነው፡፡ በይ እናቴ በአገርኛው ደግሞ፣ በአካል
በአይነ ስጋ እስክንገናኝ ድረስ ቸር ሰንብቺ፡፡ እስከዛው ግን ሰላምታዬ በአይር ይድረስሽ ብያለሁ ውድ እናቴ-ሉሲ፤ ሎንግ ሊቪ ሉሲ!
ሎንግ ሊቭ ኢትዮጲያ!
Subscribe to:
Posts (Atom)